Saints Era - Volume 1

Saints Era - Volume 1

by Ermias Tilahun
Saints Era - Volume 1

Saints Era - Volume 1

by Ermias Tilahun

Paperback(Saints Era Volume 1 ed. Large Print)

$20.00 
  • SHIP THIS ITEM
    Qualifies for Free Shipping
  • PICK UP IN STORE
    Check Availability at Nearby Stores

Related collections and offers


Overview

የቅዱሳን ዘመን ስንል ምን ማለታችን ነው?

በጌታ በኢየሱስ ክርስቶር ሞት ተዋጅተን በትንሣኤው ዳግም የተወለድን ሁላችን፣ አምነን የዳንን አማኞች ብቻ ሳንሆን ቅዱሳን ለመሆን ተጠርተናል (ሮሜ 1፡7 ፥ 1ቆሮ 1፡2)። ቅዱሳን ማለት ለጌታ ለራሱ የተለዩ ገንዘቡ የሆነ ሕዝብ ማለት ነው (ቲቶ 2፡14)። ቅዱሳንነት ጥሪ እንጂ ስም አይደለም። ይህም ጥሪ ለጥቂቶች ብቻ የተሰጠ ሳይሆን፣ በጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅነት ላመኑ ሁሉ የተሰጠ ጥሪ ነው። ቅዱሳን ለመሆን እንደተጠራን የነገረን የእግዚአብሔር ቃል፣ መጠራት ብቻ ሳይሆን በተጠራንበትም መጠራት መመላለስ እንዳለብንም ያሳስበናል (ኤፌ 4፡1)። ስለዚህም ነው ቅዱሳን የሚለው ቃል መጠሪያ ብቻ ያልሆነው።

ስለዚህ የቅዱሳን ዘመን ብለን ስንናገር፣ በቅድሚያ፣ ያመንን ሁሉ፣ ቅዱሳን (የተለዩ) ለመሆን ሁላችን እንደተጠራን እውቀቱ እንዲኖረንና በተጨማሪም በተጠራንበት መጠራት መመላለስ ደግሞ ሁላችን እንደሚጠበቅብን ግንዛቤ ውስጥ እንድናስገባም ነው። እነዚህን ሁለት ነገሮች መረዳትና በእነዚህ መረዳቶችም መመላለስ የቅዱሳንን ዘመን ማምጣት ብቻ ሳይሆን፣ የቅዱሳን ዘመን መምጣት አብሳሪዎች እንድንሆንም ያነቃቃል።

ይህ የመጀመርያ ቅጽ በሦስት ክፍሎች የተከፈለ ሲሆን፣ የመጀመርያው ክፍል የእግዚአብሔርን ቅዱስነት በተመለከተ የሚናገር ነው። ስለ ቅዱሳን ከመናገራችን በፊት የእግዚአብሔርን ቅዱስነት ማየትና መመልከት አስፈላጊ ነው። በሁለተኛው ክፍል ስለ ቅዱሳን ወይም ስለ ቅዱስ ሕዝብ እንመለከታለን። ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር ነው ቅዱስ ሕዝብ ሊኖረው የሚችለው። እንዲሁም በመጨረሻው ክፍል ላይ በተለያየ ዘመን እግዚአብሔር የተለያየ የሥራ ትኩረት ሊኖረው ስለሚችል አሁን ያለው የሥራ ትኩረት ለማየት ዘመኑን ስለማወቅ እንመለከታለን። ዘመኑን ካላወቅን አሁን ያለንበትን ዘመን የቅዱሳን ዘመን ነው ልንል አንችልም። መልካም ንባብ!


Product Details

ISBN-13: 9781087922379
Publisher: Indy Pub
Publication date: 09/10/2018
Series: Saints Era , #1
Edition description: Saints Era Volume 1 ed. Large Print
Pages: 208
Product dimensions: 6.00(w) x 9.00(h) x 0.44(d)
Language: Amharic
From the B&N Reads Blog

Customer Reviews