Arganon

Arganon

by gadeal 72
Arganon

Arganon

by gadeal 72

eBook

$3.99 

Available on Compatible NOOK Devices and the free NOOK Apps.
WANT A NOOK?  Explore Now

Related collections and offers

LEND ME® See Details

Overview

Ethiopian Orthodox Prayer in Amharic to Holly Virgin Mary. the best & the biggest common daily prayer book.
GOD bless you!
1᎐ ባለመለየት ሶስት በተዋህዶ በአኗኗር አንድ በመለኮት ትክክል ከሰውና ከመላእክትም ዘንድ አንድ ስግደት በሚሰገድለት በእግዚአብሔር ስም አምነን ይህንን አርጋኖን የሚባል የምስጋና መጽሐፍ እንጽፋለን።
2᎐ይኸውም የምስጋና መሰንቆ የቅዳሴም እንዚራ። አምላክን የወለደች በእብራይስጥ (ማሪሃም) የተባለች መርገመ ስጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት በረከተ ስጋ በረከተ ነፍስን የምታሰጥ የእመቤታችን የማርያምን ድንግልናዋን የማድነቅ መጽሐፍን እንጽፋለን።
3᎐ክብሯንና ገናንነቷንም የመናገር ስሟንም የማክበር ቅድስናዋንም የማመስገን ለንግስትነቷም መገዛት እንዲገባ የሚናገር መጽሐፍ እንጽፋለን።
4᎐አምላክን የወለደች እመቤታችን ይኽችውም የወርቅ መሰላል ናት ከሚያሰጥመው ባህር ማዕበል ሞገድ የተነሳ የማትነቀነቅ።
5᎐ መልኅቆቿም በሦስቱ ሥላሴ የተሸረቡ ገመዶች ናቸው አይቆረጡም ይኽችውም ደግሞ ከነፋሳት ኃይል የተነሣ የማትነቀነቅ በጭንጫ ላይ ያለች የእንቁ ባህሪይ ምሰሶ ናት። እሷንም የተጠጋ መውደቅ መሰናከል የለበትም።
6᎐ አቤቱ የልቦናዬን ደጅ ክፈት መንፈሳዊው ርግብ መንፈስ ቅዱስ በየዋህነቷ በርግብ ስለ ተመሰለችው የእመቤታችንን ምስጋና ኃይለ ቃሉን ያሳስበኝ ዘንድ እንዲገባ።
7᎐አቤቱ የጆሮዬንም መስኮት ክፈት ከመንፈስ ቅዱስ አንደበት የሚሰማውን የድንግልን የምስጋናዋን ሹክሹክታ ያደምፅ ዘንድ።
8᎐ አቤቱ ሆይ ያይኔን ጽጋግ ግለጽ የብርሃን እናቱ የምትሆን የእመቤታችንን ምስጋና ምስጢሩን እመለከት ዘንድ።
9᎐ዳግመኛ አንደበቴን ክፈት አቤቱ ለእግዚአብሔር እናት እመቤታችን ለድንግልናዋ ምስጋና።
10᎐የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ያቃጠለውን የኦሪትንና የነቢያትን መጻሕፍት ቃል አጽፎ እስኪጨርስ ድረስ ዓርባ ቀን ሙሉ ሳይሰወርበት የዕዝራን አንደበት የገለጽህ ሆይ እኔንም ደግሞ እንደርሱ እርዳኝ። የአብ ሙሽራ የምትሆን የእመቤታችንን ምስጋና ለመጻፍ እንድጀምር (ዕዝ 7 ፤ 6)
11᎐ጀምሮ ከመተው አድነኝ አቤቱ እርሱንም ለመፈጸም አሰልጥነኝ ከንፈሮቼንም እንደ በገና አድርጋቸው ለሚሰሙት ያማረውን የተወደደውን ምሥጢር እንዲናገሩ የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ይቃኛቸው።
12᎐አንደቤቴን እንደ ማሰንቆ አድርገው በጎውንም ያማረውን የተወደደውን መዝሙር እንዲያቀነቅን የመንፈስ ቅዱስ ድኅንፃ ይደርድረው የሚያዳምጡትም እርሱን በመስማት ፈጽመው ደስ ይሰኙ።
13᎐ሐሳባቸውም ወደታች ያይደለ ወደላይ ይመሰጥ ጽድቅንም ያስቡ። ኃጢአትን ያይደለ ጽድቅን ያስቡ ርኩሰትን ያይደለ ንጽሕናን ያስቡ።
14᎐የዋህነትንም ያስቡ። ሽንገላን ያይደለ ትሕትናንም ያስቡ። ትዕቢትን ያይደለ ፍቅርንም ያስቡ። ቅናትን ያይደለ።
15᎐ልባምነትንም ያስቡ። ስንፍናን ያይደለ ክብርንም ያስቡ። ጉስቁልናን ያይደለ የሰማዩን ያስቡ። የምድሩን የማያረጀውን ያስቡ። የሚያረጀውን ያይደለ የማይጠፋውን ያስቡ የሚጠፋውን ያይደለ።
16᎐ይህንን መጽሐፍ የሚያነብ ሁሉ አንደበቱ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የተጣፈጠ ከማርም ወለላና ከሦከር ምንጭ ይልቅ የተጣፈጠ ይሁን።
17᎐በዚህች ጸሎት የሚጸልይ ሁሉ የህይወት እሳትን በሚዳስስ እጅሽ በረከት የተባረክ ይሁን። የመንፈስ ቅዱስ መዓዛም በተዋሀደው አንደበትሽ የተመረቀ ይሁን።
18᎐ዓለምን ሁሉ በያዙ በሥላሴ እጅ የተባረከ ይሁን። ጸሎቱም ነገር በማብዛት የሚሰማቸው እንደሚመስላቸው እንደ ጸሐፍት ፈሪሳውያን ጸሎት አይሁን። (ማቴ 6 ፣ 7 ፣ 23 ፣ 14)
19᎐ ባባቱ ጆሮ በለኆሳስ እንደሚናገር እንደ ተወደደ እንዳንድ ልጅ ነገር ይሁን እንጂ። አባቱም የልጁን ነገር በደስታ ለመቀበል ጸጥ ብሎ እንደሚሰማው። እንደሚያዳምጠውም። እንዲሁ ደግሞ የሁሉ ጌታ እግዚአብሔር በዚች ጸሎት የሚጸልየውን ሰው ልመናውን ይስማ።


Product Details

BN ID: 2940152962505
Publisher: gadeal 72
Publication date: 12/31/2014
Sold by: Smashwords
Format: eBook
File size: 277 KB
Language: Amharic
From the B&N Reads Blog

Customer Reviews